የኖርዌይ ወንዶች በዓለም ላይ ምርጥ ወንዶች ናቸው ብዬ አስብ ነበር። ግን ያ እውነት አይደለም! ባለቤቴ የሆነውን ሰው ከማግኘቴ በፊት ባንኮክ ውስጥ በሚገኝ ፋብሪካ ውስጥ እሠራ ነበር። እሱም በፓታያ ይኖር ነበር። በኢንተርኔት ተገናኝተን በመጨረሻ ጥንዶች ሆንን።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለመጋባት ወሰንን። የመጣሁት ከድሃ ቤተሰብ ነው። ስለዚህ ቤተሰቤን የሚያስተዳድር የውጭ አገር ባል ማግኘቴ እሱን ለማግባት አንዱ ምክንያት ነበር።
ወደ ኖርዌይ ተዛወርን እና ኖርዌይኛ ለመማር ትምህርት ቤት መሄድ ጀመርኩ። አስቸጋሪ ጊዜ ነበር። የመንጃ ፍቃድ አልነበረኝም። እናም ባለቤቴ በመኪና ወደ ትምህርት ቤት ይዞኝ ይሄዳል፣ ይጠብቀኝ እና ተመልሰን በመኪና መውሰድ ነበረበት። በእያንዳንዱ መንገድ አንድ ሰዓት ነበር። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ወደ ሚቀርበን ቀየርን። እሱ ግን አሁንም ወደ ትምህርት ቤት መውሰዱን ኣልተወም። ብቻዬን እንድሄድ አልፈለገም።
ኖርዌይ ከመጣሁ ጀምሮ ምንም ገንዘብ የለኝም። አንድ ጊዜ ባለቤቴ ለምሳ ገንዘብ ሰጠኝ። ነገር ግን በጣም ትንሽ ገንዘብ ስለነበር ኣስቀመጥኩት። በትምህርት ቤት ያሉ ጓደኞቼ ሥራ እንዳገኝ ሊረዱኝ ይፈልጋሉ። ባለቤቴ ግን እንደማልችል ነገረኝ። እንደ ጽዳት መሥራት ለእኔ ተገቢ ነው ብሎ አያስብም።
ይልቁንም ለእኔ ሌላ ሥራ ሰጠኝ። ጋራዥ መሥራት። እሱ አለቃ ነበር እኔ ደሞ ሁሉንም ነገር እሰራለው። ስለታመመ ብዙ መሥራት አልቻለም። ጋራዡን በመገንባት ካገኘው ገንዘብ ምንም አልሰጠኝም።
አንድ ቀን እቤት ብቻውን ሲሆን አንደሚደብረው እና ስለዚ ውሻ አንደሚያስፈልገን ወሰነ። እኔ ደሞ ከትምህርት በኋላ ስለሚደከምኝ እና የቤት ስራ ስላለኝ ውሻ አልፈልግም። ውሻውን በየቀኑ ውጪ አንደሚያወጣው ነግሮኛል ነገር ግን በመጨረሻ ውሻውን እና ሽማግሌ ባለቤቴን መንከባከብ ግድ ሆነብኝ።
ወደፊት ምን እንደሚያመጣ አላውቅም። እቅዴ ወደ ሌላ ትምህርት ቤት መሄድ ነው። ነገር ግን ባለቤቴ ያንን እንዳደርግ አይፈልግም። እኔን አስቸጋሪ ለማድረግ የበለጠ ርቆ ለመሄድ እያሰበ ነው። መታገስ አፈልጋለው ግን አንዴት አንደሆነ አላውቅም። እኔ እንዳሰብኩት ባዕድ አገር ከሽማግሌ ጋር መኖር ቀላል አይደለም።