Ladda ner PDF
Tillbaka till listan med berättelser

የአጎስቲኖ ታሪክ

Skriven av LIDA Italia

Illustrerad av Billie Cejka Risnes

Översatt av Loza Tadesse Mamo

Uppläst av Dawit Leykun

Språk amhariska

Nivå Nivå 5

Läs hela berättelsen

Reading speed

Automatisk avspälning


ስሜ አጎስቲኖ ይባላል 51 ዓመቴ ነው። ስራዬ በብስክሌት ምግብ ማድረስ ነው። ሁለት ሴት ልጆች አሉኝ ግን ብዙም ኣናወራም። እኔና እናታቸው አብረን አንኖርም ምክንያቱም ተፋተናል።


ከፍቺ በኋላ የቤት ኪራይ መክፈል ስለማልችል ከእናቴ ጋር ነው የምኖረው። በዚህ ከተማ ውስጥ ኪራይ በጣም ውድ ነው።


ከጥቂት ወራት በፊት በአንድ ኩባንያ ውስጥ በጽዳት ሠራተኛነት እሠራ ነበር። የተበላሹ ነገሮችን አስተካክያለሁ፣ ሳጥኖች እሸከማለው እና ማንም በፈለገው ጊዜ እረዳ ነበር። አንድ ቀን ድርጅቱ አባረረኝ። ለምን እንደሆነ አልገባኝም።


ብዙ ሰዎች በብስክሌት ምግብ ሲያቀርቡ አየሁ። ብስክሌት መንዳት ስለምችል የአንድ ትልቅ ማጓጓዣ ድርጅት በር አንኳኳሁ። ለእያንዳንዱ ማድረስ ሦስት ዩሮ ሰጡኝ። በቀን 40€ አገኛለሁ። በጣም እድለኛ ከሆንኩ 60€ እና ደንበኞቼ የኪስ ይሰጡኛል።


የበዓል ቀን ክፍያ የለም፣ ስትታመም ክፍያ የለም፣ ባጠቃላይ ምንም አይነት መብት አላገኘሁም። ትክክል አይመስለኝም ግን ስራውን እፈልጋለሁ። አብዛኛዎቹ ሌሎች ሰራተኞች ከመላው አለም የመጡ ስደተኞች ናቸው።


ብዙ የዴሊቨሪ ሠራተኞች በየቀኑ በአደጋ ይጎዳሉ። ከዚያም አንድ የ25 ዓመት የዴሊቨሪ ሠራተኛ በመኪና ተገጭቶ ሲሞት ባለ ሥልጣናቱም እኛን ልብ ማለት ጀመሩ። ይህ ከመሆኑ በፊት መሞቱ አሳፋሪ ነው።


ከሌሎች ኩባንያዎች ከመጡ ሰዎች ጋር በመሆን ከአካባቢው ዩኒየን ጋር ስለሠራተኞች መብት ኮርስ ወሰድኩ። የሕግ ምክር በነጻ ሰጡን። የበለጠ እውቅና እና መብት ለማግኘት ታግለናል።


ከረዥም ጊዜ በኋላ ድካማችን ሁሉ ፍሬያማ ሆነ። አንድ ትልቅ የዴሊቨሪ ድርጅት ከፍተኛ ቅጣት መክፈልና ለሠራተኞች ቋሚ ሥራ መስጠት ነበረበት። በአለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ ሲከሰት ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ነገሮች መሻሻል የጀመሩ ይመስላል።


Skriven av: LIDA Italia
Illustrerad av: Billie Cejka Risnes
Översatt av: Loza Tadesse Mamo
Uppläst av: Dawit Leykun
Språk: amhariska
Nivå: Nivå 5
Creative Commons Licens
Detta verk är licensierat under en Creative Commons Erkännande 4.0 Internationell Licens.
Valmöjligheter
Tillbaka till listan med berättelser Ladda ner PDF