ዩሊያና ባለቤቷ እና ትንሽ ሴት ልጃቸው በዩክሬን ውስጥ ጸጥ ባለች ትንሽ መንደር ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዩሊያ በየማለዳው በአእዋፍ ድምፅ መንቃት ትወድ ነበር። እርሷም ከቤት ርቄ እኖራለሁ ወይም በጠዋቱ የወፍ ድምፅ ሳይቀሰቅሰኝ እነሳለሁ ብላ በፍፁም አስባ አታውቅም።
ባለቤቷ በቂ ገንዘብ ስለሌለው ሁል ጊዜ ያማርር ነበር እና በጣም መጠጣት ጀመረ። በፖርቱጋል እድላቸውን ለመሞከር ወሰኑ። ምናልባት እዚያ ቤት ለመሥራት እና ለቤተሰባቸው የተሻለ የወደፊት ሁኔታ ለመፍጠር ተጨማሪ ገንዘብ ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል።
ዩሊያ ከአዲሱ ቤቷ ጋር በጥሩ ሁኔታ ተስማማች። የጽዳት ስራ መሥራት ጀመረች። ደንበኞቿ በትጋት መሥራቷን እና ጨዋነቷን ያደንቃሉ። በሌላ መልኩ ባሏ የበለጠ እንደተገለለ ተሰማው። በመጠጥ ችግር ምክንያት አሠሪዎች አላመኑትም እና ሥራ አይሰጡትም።
አንድ ቀን ዩሊያን ላይ መጮህ ጀመረ። ከዚያም መግፋት ጀመረ። ጩኸቱና ድብደባው ተባብሷል በተለይ ሰክሮ ነበር። ዩሊያ ለራሷ እና ለሴት ልጇ ፈራች። ግን ምን ማድረግ እንዳለባት አላወቀችም።
በመጨረሻ ዩሊያ በሆስፒታሉ ውስጥ ወደሚገኝ ድንገተኛ ክፍል በተሰበረ ክንድ መሄድ ኣስፈለጋት። የቤት ውስጥ ጥቃት በፖርቱጋል ውስጥ ትልቅ ችግር እንደሆነ ነገሯት። ወንጀል ነውና ለፖሊስ ማሳወቅ ኣለብሽ ሲሉም ነገሯት።
ዩሊያ ደክሟት ነበር እና ትንሽ ሴት ልጇ በየእለቱ ሁከት በምታይበት ቤት ውስጥ እንድታድግ አልፈለገችም። ዩሊያ በጣም በተለያዩ መልኮች ቤትዋ ውስጥ የመጎሳቆል በደሎች ሁሌም ይደርሱባት እንደነበር ተገነዘበች።
ዩሊያ ከረጅም ጊዜ በፊት ካገኘችው የበለጠ ደህንነት ወደሚሰማት የሴቶች መጠለያ ሄደች። በጠዋት በወፍ ድምፅ ከእንቅልፏ ከነቃችበት ጊዜ ወዲህ እንደዚህ አይነት ስሜት ኣልተሰማትም።