Ladda ner PDF
Tillbaka till listan med berättelser

መውለድ

Skriven av LIDA Norge

Illustrerad av Sara Dorthea Johannesen

Översatt av Loza Tadesse Mamo

Uppläst av Dawit Leykun

Språk amhariska

Nivå Nivå 4

Läs hela berättelsen

Reading speed

Automatisk avspälning


ሰላማዊት 29 አመቷ ነው። የመጀመሪያ ልጇን ኤርትራ ውስጥ ወለደች። እሷና ቤተሰቧ እዚያ በጣም ስለተቸገሩ ወደ ጣሊያን ለመሄድ ወሰኑ።


ኢንጋ ገና 19 ዓመት ሳይሞላት በፊት ከቤት ወጣች። ወደ ኖርዌይ ሄዳ የመጀመሪያ ልጇን እዚያ ወለደች።


ሰላማዊት ሁለተኛ ልጇን ባረገዘች ጊዜ ሌላ ሀገር ልጅ መውለድ ምን ሊመስል እንደሚችል አሠበች።


ሰላማዊት እና ኢንጋ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ናቸው። ሰላማዊት የመውለድ ልምድ ስላላት ደህንነት ተሰምቷታል። ኢንጋ ስለ መውለድ እናቷን ኣናገረች።


ሁለቱም ሴቶች በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ አገሮች ነፍሰ ጡር እናቶች የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ የማግኘት መብት እንዳላቸው ሰምተው ነበር። ይህ ማለት በእርግዝና ወቅት እርዳታ ያገኛሉ ማለት ነው። ሰላማዊት መፀነሷን እንዳወቀች ከዶክተሯ ጋር ቀጠሮ ያዘች። የሰላማዊት ባል በመኪና ወደ ሐኪም ወሰዳት።


ሐኪሙ አንዳንድ ምርመራዎችን ካደረገ በኋላ ሰላማዊት አንዳንድ ነፍሰ ጡር እናቶች የሚይዘው የስኳር በሽታ እንዳለባት አወቀ። ጤናማ ምግብ መመገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ነበረባት። ሰላማዊት እሷና ልጇ ከመታመማቸው በፊት ዶክተር ጋር ቀድማ በመሄዷ ተደሰተች።


የኢንጋ ጎረቤት ልጅ ለመውለድ እየሞከረች እንደሆነ ስትሰማ ጎረቤቷ እንዳረገዘች ዶክተር እንድትሄድ በፍጥነት ነገሩዋት። በዚህ መንገድ እሷ እና ልጇ ጤናማ መሆናቸውን ማረጋገጥ ትችላለች። ዶክተሩ ለነፍሰ ጡር ሴቶች ጠቃሚ የሆነውን ፎሊክ አሲድ የተባለውን ቫይታሚን እንድትወስድ ነገራት።


ኢንጋ እና ሀኪሟ በእርግዝናዋ ወቅት መደበኛ ምርመራ ለማድረግ አዋላጅ ነርስ እንድታገኝ ተስማሙ። አዋላጇ ስለ ምግብ እና እረፍት እንዲሁም እራሷን እና ልጇን እንዴት ደህንነት እና ጤንነቷን መጠበቅ እንዳለባት መረጃ ሰጣት።


ሁለቱም ሴቶች ጤናማ ልጆችን ወለዱ። ሰላማዊት ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች። ኢንጋ ደሞ ሴት ልጅ ወለደች። ባሎቻቸው በጣም ኩሩ ነበሩ፣ እናም ለሚያውቋቸው ሁሉ ስለ ጠንካራ ሚስቶቻቸው እና ጤናማ ልጆቻቸው ያወሩ ነበር።


Skriven av: LIDA Norge
Illustrerad av: Sara Dorthea Johannesen
Översatt av: Loza Tadesse Mamo
Uppläst av: Dawit Leykun
Språk: amhariska
Nivå: Nivå 4
Creative Commons Licens
Detta verk är licensierat under en Creative Commons Erkännande 4.0 Internationell Licens.
Valmöjligheter
Tillbaka till listan med berättelser Ladda ner PDF