አሊሻ ሥራ መፈለግ አለባት ምክንያቱም ቤተሰቧ ለምግብ እና ለልብስ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል።
አሊሻ በትውልድ አገሯ ስራ አልሰራችም፣ ግን ምግብ በማብሰል ጥሩ ነች እና ከሰዎች ጋር ማውራት ትወዳለች።
ምናልባት ምግብ ቤት ውስጥ ልትሰራ ትችል ይሆናል? አሊሻ ድህረ-ገፅ ላይ የተለጠፈ ሥራ ትፈልጋለች።
ለሼፍ ማስታወቂያ ታገኛለች። ምግብ ቤት ውስጥ ለሚያበስል ሰው ነው የሚፈልጉት።
ለስራ ቃለ መጠይቁ ትሄዳለች። የምግብ ቤቱ አስተዳዳሪ እንደ ሼፍ የሰለጠነ ሰው እንደሚፈልጉ ነገሯት።
አሊሻ ተስፋ ቆርጣለች ነገር ግን “ምግብ እና መስተንግዶ” የሚባል ኮርስ ወሰደች። ይህ በአንድ ሬስቶራንት ውስጥ ሥራ እንድታገኝ ይረዳኛል የሚል ተስፋ ኣላት።
ኣሊሻ የሥልጠና ኮርሷ አካል ሆኖ ሬስቶራንት ውስጥ መሥራት አለባት። የደመወዝ ክፍያ አታገኝም ግን የሥራ ልምድ ታገኛለች።
የትምህርቱን ዝርዝሮች በሲቪዋ ላይ ጨምራለች። ሲቪ የሰራቻቸው ስራዎች እና የወሰደቻቸው ኮርሶች ሁሉ መግለጫ ነው።
በሚቀጥለው ጊዜ አሊሻ በአንድ ሬስቶራንት ውስጥ ለስራ ቃለ መጠይቅ ስትሄድ ስራው ይሰጣታል። ከባድ ስራ ነው። ብዙውን ጊዜ ምሽት ላይ ልጆቿ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ መሥራት አለባት።
በራሷ ገንዘብ ለቤተሰቧ ምግብና ልብስ መግዛት የሚያስችል ሥራ በማግኘቷ ኩራት ይሰማታል።