ስሜ ማሊክ ይባላል 39 አመቴ ነው። የተወለድኩት አፍጋኒስታን ነው። የኔ ሃይማኖት ከአፍጋኒስታን ዋና ሃይማኖት የተለየ ነው።
ለብዙ ዓመታት የእኔ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ሰዎች ስደት ደርሶባቸዋል። ይህ ለቤተሰቤ በጣም ከባድ ነበር።
ከጥቂት አመታት በፊት ጦርነት ነበር። እኔም እንዳልገደል ፈራሁ። ቤተሰቤን ትቼ ወጣው አውሮፓ ለመሄድ እና ኣዲስ ህይወት ለመጀመር።
ለብዙ ኪሎ ሜትሮች በእግር ተጓዝኩ። አንዳንድ ጊዜ ምንም ምግብ አልነበረኝም እናም የማርፍበት ቦታ አልነበረኝም። አብሬያቸው የተጓዝኳቸው አንዳንድ ሰዎች ሞተዋል።
በመጨረሻ ደረስኩ። የረዱኝ አንዳንድ የሀገሬ ሰዎች አገኘሁ። ያለ እነርሱ ምን እንደማደርግ ኣላውቅም ነበር።
ቋንቋውን መማር ጀመርኩ ግን ከባድ ነበር። ሥራ ለማግኘት ቋንቋውን መናገር አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁ።
መጀመሪያ ላይ ቋንቋውን ለመማር ለበርካታ ዓመታት አጠናሁ። ከባድ ነበር ነገር ግን አዳዲስ ነገሮችን መማር ያስደስተኛል።
ካጠናሁ በኋላ መሥራት ጀመርኩ። መጀመሪያ ሬስቶራንት ውስጥ ሰራሁ። ከዛ ሌሎችን መርዳት ስለምፈልግ አስተማሪ ሆንኩ።
አንድ ቀን ወደ አፍጋኒስታን ለመመለስ ተስፋ አደርጋለሁ። እዚያ ያሉ ብዙ ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። እና እነርሱን መርዳት እፈልጋለሁ።