“አዎ እኔና ባለቤቴ ሁለት ሴት ልጆች እና አንድ ወንድ ልጅ አሉን።”
「はい、私と夫には娘がふたり、息子がひとりいます」
“እኔም ሁለት ሴት ልጆች አሉኝ፣ ግን ተፋትቻለሁ።”
「私にもふたりの娘がいますが、夫とは別れました」
“ሚና የአራት አመት ልጅ ነች ወደ ቅድመ ትምህርት ቤት ትሄዳለች። ሚርያም አስር ነች። ስለዚህ ወደ መደበኛ ት/ቤት ትሄዳለች።”
「ミナは4歳です。ようちえんに通っています。ミリアムは10歳で、学校に通っています」
“ሁሉም ልጆቼ ትምህርት ቤት ናቸው። ልጄ በሚቀጥለው ዓመት ይመረቃል።”
「私の子どもたちはみんな学校に通っています。息子は来年、卒業します」
“በጣም ጥሩ ነው! እነሱ በፍጥነት አደጉ። ከዚያ በኋላ ምን ማድረግ ይፈልጋል?”
「おめでとうございます!子どもたちの成長はとても早いですね。息子さんは卒業したあとに、何をしたいのですか?」
“ስራ ማግኘት ይፈልጋል። ነገር ግን በምትኩ ዩኒቨርሲቲ መግባት እንዳለበት ነግሬዋለሁ።”
「息子は働こうと考えていますが、私は息子に、大学に進学したほうがいいと伝えています」
“ይህ ጥሩ ሀሳብ ነው። እኔም ልጆቼ አንድ ቀን ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ተስፋ አደርጋለሁ።”
「いい考えですね。私も子どもたちには、いつか大学で学んでほしいと思っています」