ካርሎስ ስኩተር ይነዳል። በፍጥነት ይነዳል።
カルロスはスクーターに乗っています。速く走らせています。
በመንገዱ ላይ ውሃ አለ። መንገዱ አንሸራታች ነው።
道路に水たまりがあります。道路は滑りやすいです。
አንዲት ሴት፣ አምቡላንስ ትጠራለች። “አደጋ ተፈጥሯል ቶሎ ኑ! ኣለች።”
女性が救急車を呼びます。「事故がありました。すぐに来てください!」
ሁለት ሰዎች ካርሎስን በቃሬዛ ላይ አስቀመጡት።
2人の男性がカルロスを担架にのせます。
አንዲት ነርስ ካርሎስን ወደ ሆስፒታል ውስጥ ወሰደችው።
看護師がカルロスを運んで病院に入ります。
የካርሎስ እግር በጣም ያማል እናም ተጨነቀ።
カルロスは足がひどく痛むので、心配しています。
ሁለት ዶክተሮች እግሩን ቀዶ ሕክምና አደረጉለት።
二人の医者が足の手術をします。
ወላጆቹ ጎበኙት። አደጋው እንዴት እንደተከሰተ ጠየቁት።
カルロスの両親がお見舞いに来ます。事故がどのようにして起きたか聞きます。
ወደ ቤት ወሰዱት። ካርሎስ ክራንች እየተጠቀመ ነው።
カルロスを車で家に連れて帰ります。カルロスは松葉づえを使っています。