ቶም የጥርስ ሕመም አለበት። ጥርሱ በጣም ያመዋል።
Tom has a toothache. His tooth hurts very much.
የጥርስ ሐኪም ማየት ያስፈልገዋል። ነገር ግን በመጀመሪያ ለሥቃዩ አንድ ነገር ያስፈልገዋል።
He needs to see his dentist, but first he needs something for the pain.
በአቅራቢያው ወደሚገኝ ፋርማሲ ነዳ።
He drives to the nearest pharmacy.
“የጥርስ ሕመም አለብኝ” አለ። “ለዚህ የሚሆን ነገር አለህ?”
“I have a toothache,” he says. “Do you have anything for that?”
“አዎ፣ እዚህ አንዳንድ የህመም ማስታገሻዎች አሉ። ለእነዚህ ማዘዣ አያስፈልግም።”
“Yes, here are some painkillers. You don’t need a prescription for these.”
“አመሰግናለሁ! ስንት ነው ዋጋው?”
“Thank you. How much do they cost?”
“ዋጋው ዘጠኝ ዩሮ ነው። ነገር ግን የጥርስ ሐኪም ማየት አለብዎት።”
“They cost nine euros. But you should see a dentist.”
“እሺ! ነገ ጠዋት የጥርስ ሀኪሜን እደውልለታለው።”
“Okay, I will call my dentist tomorrow morning.”
“ጠንካራ መድሃኒት ከፈለጉ ከጥርስ ሀኪምዎ ወይም ከዶክተርዎ ማዘዣ ማግኘት ያስፈልግዎታል።”
“If you need stronger medicine, you will need to get a prescription from your dentist or doctor.”